ማሳሰቢያ፡ ፋብሪካው ገና ምርት አልጀመረም። አሁን የምንቀበለው የፍላጎት ምዝገባ ብቻ ነው።

ምርቶቻችን

አራት ዓይነት የተፈጨ (ማሽ) መኖ ለማዘጋጀት አቅደናል። ፋብሪካው ገና ስላልጀመረ አራቱም «በቅርቡ» ናቸው።

በእጅ የተያዙ የበቆሎ እሸቶች
ፎቶዎቹ ገላጭ ናቸው፤ የኑትሮጵያን ቦታ፣ ፋብሪካ፣ ሠራተኞች ወይም ምርት አያሳዩም።
ሦስት እንቁላሎች
በቅርቡ

የእንቁላል ዶሮ መኖ

እንቁላል ለሚጥሉ ዶሮዎች።

በሣር ላይ የቆመች ዶሮ
በቅርቡ

የሥጋ ዶሮ መኖ

ለሥጋ ለሚያድጉ ዶሮዎች።

በእጅ ላይ የተያዘች ጫጩት
በቅርቡ

የቄብ ዶሮ መኖ

እንቁላል ከመጣል በፊት ላሉ ወጣት ዶሮዎች።

ላሞችና ጥጃ በግጦሽ ላይ
በቅርቡ

የወተት ላም መኖ

ወተት ለሚሰጡ ላሞች።

ስለ ዋጋና ዝርዝር

ዋጋ፣ የንጥረ ነገር መጠን ወይም የአመጋገብ መጠን በዚህ ገጽ ላይ አላስቀመጥንም። ገና ስላልወሰንናቸው ነው። ስንወስን በዚሁ ገጽ ላይ እናወጣለን፤ ፍላጎታቸውን ላስመዘገቡ ደግሞ በቀጥታ እንነግራለን።

የመኖው መጠን በ50 ኪሎ ግራም ከረጢት ነው። ሁለት ከረጢት አንድ ኩንታል ነው።

በየወሩ ምን ያህል መኖ ያስፈልግዎታል?

ምዝገባው ነፃ ነው፤ ምንም ክፍያ የለውም። የሚሰጡን መረጃ የሚያገለግለው ለዕቅዳችንና እርስዎን ለማግኘት ብቻ ነው።