ማሳሰቢያ፡ ፋብሪካው ገና ምርት አልጀመረም። አሁን የምንቀበለው የፍላጎት ምዝገባ ብቻ ነው።

የግላዊነት መግለጫ

ይህ ገጽ በዚህ ድረ ገጽ ላይ የሚሰጡንን መረጃ እንዴት እንደምንይዘው ይገልጻል።

የምንሰበስበው መረጃ

በምዝገባ ቅጽ የሚሞሉትን ብቻ፦ ስም፣ ስልክ ቁጥር፣ አካባቢ (ክልል፣ ዞን፣ ወረዳ፣ ቀበሌ)፣ የገበሬና የዶሮ ዓይነት፣ የዶሮ ብዛት፣ በወር የሚያስፈልግ የመኖ መጠን፣ መቼ እንደሚያስፈልግዎት፣ እና በምን መንገድ እንድናገኝዎት እንደሚፈልጉ። ለአከፋፋዮች ደግሞ የንግዱን ስም፣ የማከማቻ አቅምና ልምድ።

ለምን እንደምንሰበስበው

ሁለት ነገር ብቻ፦ ስለ መኖ ፍላጎትዎ እርስዎን ለማነጋገር፣ እና ምን ያህል መኖ ማዘጋጀት እንዳለብን ለማቀድ።

ለማን እንደምንሰጠው

ለማንም አንሸጥም፤ ለማስታወቂያ ድርጅት አንሰጥም። ከኑትሮጵያ ሠራተኞች ውጭ ለሌላ ወገን አናጋራም።

ስለዚህ ድረ ገጽ

በዚህ ድረ ገጽ ላይ የክትትል ኩኪ (cookie) ወይም የማስታወቂያ መከታተያ አልተጫነም። የግል መረጃዎ በድረ ገጹ አድራሻ (URL) ውስጥ አይቀመጥም።

ምን ያህል ጊዜ እንደምንይዘው

ስለ መኖ አቅርቦት እስካላነጋገርንዎት ወይም እንዲሰረዝ እስኪጠይቁን ድረስ።

መብትዎ

ስለ እርስዎ የያዝነውን መረጃ እንድናሳይዎት፣ እንድናስተካክል ወይም ጨርሶ እንድንሰርዝ በማንኛውም ጊዜ መጠየቅ ይችላሉ። ያግኙን

ለውጥ ካለ

ይህ መግለጫ ከተቀየረ በዚሁ ገጽ ላይ እናስቀምጣለን።

ለጥያቄ

ስልክ፦ +251 911 721 641 · ኢሜይል፦ account@nutropiafood.com